ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 89:29-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።

30. “ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ደንቤን ባይጠብቁ፣

31. ሥርዐቴን ቢጥሱ፣ትእዛዜንም ባያከብሩ፣

32. ኀጢአታቸውን በበትር፣በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።

33. ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፤ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።

34. ኪዳኔን አላፈርስም፤ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።

35. አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣ዳዊትን አልዋሸውም።

36. የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 89