ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 88:9-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።

10. ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን?የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ

11. ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣ታማኝነትህስ እንጦርጦስ ይነገራልን?

12. ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን?

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።

14. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን ታርቀኛለህ?ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?

15. እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ።

16. ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤መዓትህም አጠፋኝ።

17. ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤በአንድነትም ዙሪያዬን አጥረው ያዙኝ።

18. ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 88