ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 88:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የቊጣህ ክብደት በላዬ ዐርፎአል፤በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል። ሴላ

8. የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችል፤

9. ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።

10. ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን?የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ

11. ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣ታማኝነትህስ እንጦርጦስ ይነገራልን?

12. ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን?

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 88