ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 88:10-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን?የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ

11. ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣ታማኝነትህስ እንጦርጦስ ይነገራልን?

12. ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን?

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።

14. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን ታርቀኛለህ?ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?

15. እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 88