ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 88:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በቀንና በሌሊት በፊትህ አጮኻለሁ።

2. ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፤

3. ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ሕይወቴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች።

4. ወደ ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር ተቈጠርሁ፤ዐቅምም አጣሁ።

5. በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ።

6. በዐዘቅት ጥልቀት ውስጥ ጣልኸኝ፤በጨለማ ጒድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ።

7. የቊጣህ ክብደት በላዬ ዐርፎአል፤በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል። ሴላ

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 88