ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 87:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ

4. “ከሚያውቁኝ መካከል፣ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር፣‘ይህ ሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”

5. በእርግጥም ስለ ጽዮን፣“ይህም ያም ሰው በእርሷ ውስጥ ተወለዱ፤ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል።

6. እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣“ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ

7. የሚያዜሙም መሣሪያ የሚጫወቱም፣“ምንጩ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛል” ይላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 87