ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 86:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ጌታ ሆይ፤ ማረኝ፤ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና።

4. የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፤ጌታ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።

5. ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።

6. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤የልመናዬን ጩኸት ስማ።

7. አንተ ስለምትመልስልኝ፣በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።

8. ጌታ ሆይ፤ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ከአንተም ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 86