ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 86:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል፤ ስማኝም፤እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና።

2. ለአንተ የተለየሁ ሰው ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤አንተ አምላኬ ሆይ፤በአንተ የታመነብህን ባሪያህን አድን።

3. ጌታ ሆይ፤ ማረኝ፤ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና።

4. የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፤ጌታ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።

5. ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።

6. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤የልመናዬን ጩኸት ስማ።

7. አንተ ስለምትመልስልኝ፣በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።

8. ጌታ ሆይ፤ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ከአንተም ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 86