ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 85:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ማዳንህን ለግሰን።

8. እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።

9. ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው።

10. ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፤ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ።

11. ታማኝነት ከምድር በቀለች፤ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች።

12. እግዚአብሔር በጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።

13. ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 85