ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 85:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?

6. ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ማዳንህን ለግሰን።

8. እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።

9. ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 85