ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 85:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።

2. የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ። ሴላ

3. መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ።

4. መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።

5. የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?

6. ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ማዳንህን ለግሰን።

8. እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።

9. ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው።

10. ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፤ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ።

11. ታማኝነት ከምድር በቀለች፤ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች።

12. እግዚአብሔር በጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።

13. ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 85