ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 80:9-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. መሬቱን መነጠርህላት፤እርሷም ሥር ሰዳ አገሩን ሞላች።

10. ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።

11. ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ቊጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።

12. ታዲያ ዐላፊ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲለቅም፣ለምን ቅጥሯን አፈረስህ?

13. ዕርያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል።

14. የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤

15. ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል ናት።

16. እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል።

17. ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን።

18. ከእንግዲህ አንተን ትተን ወደ ኋላ አንመለስም፤ሕያዋን አድርገን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን።

19. የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 80