ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 80:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን።

7. የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

8. ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።

9. መሬቱን መነጠርህላት፤እርሷም ሥር ሰዳ አገሩን ሞላች።

10. ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።

11. ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ቊጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 80