ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 80:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤

15. ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል ናት።

16. እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል።

17. ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን።

18. ከእንግዲህ አንተን ትተን ወደ ኋላ አንመለስም፤ሕያዋን አድርገን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን።

19. የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 80