ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 79:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ያዕቆብን በልተውታልና፤መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል።

8. የአባቶቻችንን ኀጢአት በእኛ ላይ አትቍጠርብን፤ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፤በጭንቅ ላይ እንገኛለንና።

9. አዳኛችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ስለ ስምህ ክብር ብለህ እርዳን፤ስለ ስምህ ስትል፣ታደገን፤ ኀጢአታችንንም ይቅር በል።

10. ሕዝቦች፣ “አምላካቸው የት አለ?”ለምን ይበሉ?የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም በቀል፣ዐይናችን እያየ ሕዝቦች ይወቁት።

11. የእስረኞች ሰቈቃ በፊትህ ይድረስ፤በክንድህም ብርታት፣ሞት የተፈረደባቸውን አድን።

12. ጌታ ሆይ፤ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ የተዘባበቱትን መዘባበት፣ሰባት ዕጥፍ አድርገህ አስታቅፋቸው።

13. እኛ ሕዝብህ፣ የማሰማሪያህ በጎችህ፣ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ከትውልድ እስከ ትውልድም፣ውለታህን እንናገራለን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 79