ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የኤፍሬም ልጆች የታጠቁ ቀስተኞች ቢሆኑም፣በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።

10. የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፤ በሕጉም መሠረት ለመሄድ እንቢ አሉ።

11. እርሱ የሠራውን ሥራ፣ያሳያቸውንም ድንቅ ነገር ረሱ።

12. አባቶቻቸው በዐይናቸው እያዩ፣በግብፅ አገር፣ በጣኔዎስ ምድር ታምራት አደረገ።

13. ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።

14. ቀን በደመና መራቸው፤ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78