ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:61-72 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

61. የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።

62. ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ።

63. ጐልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፤ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።

64. ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው።

65. ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት ጀግናም ብድግ አለ።

66. ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤የዘላለም ውርደትም አከናነባቸው።

67. የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፤የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም።

68. ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ።

69. መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት።

70. ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ከበጎች ጒረኖ ውስጥ ወሰደው፤

71. ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣የሚያጠቡ በጎችን ከመከተል አመጣው።

72. እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78