ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:59-69 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

59. እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ።

60. በሰዎች መካከል ያቆማትን ድንኳን፣የሴሎን ማደሪያ ተዋት።

61. የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።

62. ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ።

63. ጐልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፤ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።

64. ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው።

65. ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት ጀግናም ብድግ አለ።

66. ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤የዘላለም ውርደትም አከናነባቸው።

67. የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፤የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም።

68. ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ።

69. መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78