ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:52-64 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

52. ሕዝቡን ግን እንደ በግ አወጣቸው፤በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው።

53. በሰላም መራቸው፤ እነርሱም አልፈሩም፤ጠላቶቻቸውን ግን ባሕር ዋጣቸው።

54. ቀኝ እጁም ወዳስገኘችው ወደዚህ ተራራ፣ወደ ቅድስት ምድር አገባቸው።

55. ሕዝቦችን ከፊታቸው አባረረ፤ምድራቸውን ርስት አድርጎ አከፋፈላቸው፤የእስራኤልንም ነገዶች በጠላቶቻቸው ቤት አኖረ።

56. እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት፤በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ሥርዐቱንም አልጠበቁም።

57. ተመልሰው እንደ አባቶቻቸው ከዳተኛ ሆኑ፤እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ።

58. በኰረብታ ማምለኪያዎቻቸው አስቈጡት፤ተቀርጸው በተሠሩ ጣዖቶቻቸው አስቀኑት።

59. እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ።

60. በሰዎች መካከል ያቆማትን ድንኳን፣የሴሎን ማደሪያ ተዋት።

61. የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።

62. ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ።

63. ጐልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፤ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።

64. ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78