ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:48-53 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

48. ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣የከብት መንጋቸውን ለመብረቅ እሳት ዳረገ።

49. ጽኑ ቍጣውን በላያቸው ሰደደ፤መዓቱን፣ የቅናቱን ቍጣናመቅሠፍቱን ላከባቸው፤አጥፊ የመላእክት ሰራዊትም ሰደደባቸው።

50. ለቊጣው መንገድ አዘጋጀ፤ነፍሳቸውንም ከሞት አላተረፈም፤ነገር ግን ሕይወታቸውን ለመቅሠፍት አሳልፎ ሰጠ።

51. የዐፍላ ጒልበታቸው መጀመሪያ የሆኑትን በካም ድንኳን፣በኵሮቻቸውንም ሁሉ በግብፅ ምድር ፈጀ።

52. ሕዝቡን ግን እንደ በግ አወጣቸው፤በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው።

53. በሰላም መራቸው፤ እነርሱም አልፈሩም፤ጠላቶቻቸውን ግን ባሕር ዋጣቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78