ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:47-57 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

47. የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣የበለስ ዛፋቸውንም በውርጭ አጠፋ።

48. ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣የከብት መንጋቸውን ለመብረቅ እሳት ዳረገ።

49. ጽኑ ቍጣውን በላያቸው ሰደደ፤መዓቱን፣ የቅናቱን ቍጣናመቅሠፍቱን ላከባቸው፤አጥፊ የመላእክት ሰራዊትም ሰደደባቸው።

50. ለቊጣው መንገድ አዘጋጀ፤ነፍሳቸውንም ከሞት አላተረፈም፤ነገር ግን ሕይወታቸውን ለመቅሠፍት አሳልፎ ሰጠ።

51. የዐፍላ ጒልበታቸው መጀመሪያ የሆኑትን በካም ድንኳን፣በኵሮቻቸውንም ሁሉ በግብፅ ምድር ፈጀ።

52. ሕዝቡን ግን እንደ በግ አወጣቸው፤በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው።

53. በሰላም መራቸው፤ እነርሱም አልፈሩም፤ጠላቶቻቸውን ግን ባሕር ዋጣቸው።

54. ቀኝ እጁም ወዳስገኘችው ወደዚህ ተራራ፣ወደ ቅድስት ምድር አገባቸው።

55. ሕዝቦችን ከፊታቸው አባረረ፤ምድራቸውን ርስት አድርጎ አከፋፈላቸው፤የእስራኤልንም ነገዶች በጠላቶቻቸው ቤት አኖረ።

56. እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት፤በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ሥርዐቱንም አልጠበቁም።

57. ተመልሰው እንደ አባቶቻቸው ከዳተኛ ሆኑ፤እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78