ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:41-47 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፤የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጡት።

42. እነርሱን በዚያን ቀን ከጠላት የታደገበትን፣ያን ኀይሉን አላስታወሱም፤

43. በግብፅ ያደረገውን ታምራዊ ምልክት፣በጣኔዎስም በረሓ ያሳየውን ድንቅ ሥራ አላሰቡም።

44. ወንዞቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ከጅረቶቻቸውም መጠጣት አልቻሉም።

45. የዝንብ ሰራዊት ሰደደባቸው፤ ነደፏቸውም፤ጓጒንቸርም ላከባቸው፤ ሰዎችንም አጠፉ።

46. አዝመራቸውን ለኵብኵባ፣ሰብላቸውንም ለአንበጣ ሰጠባቸው።

47. የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣የበለስ ዛፋቸውንም በውርጭ አጠፋ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78