ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:36-42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

36. ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት፤በአንደበታቸው ዋሹት።

37. ልባቸው በእርሱ የጸና አልነበረም፤ለኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም።

38. እርሱ ግን መሓሪ እንደ መሆኑ፣በደላቸውን ይቅር አለ፤አላጠፋቸውም፤ቊጣውን ብዙ ጊዜ ገታ፤መዓቱንም ሁሉ አላወረደም።

39. ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፣ሥጋ ለባሾች መሆናቸውን አሰበ።

40. በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት!በበረሓስ ምን ያህል አሳዘኑት!

41. ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፤የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጡት።

42. እነርሱን በዚያን ቀን ከጠላት የታደገበትን፣ያን ኀይሉን አላስታወሱም፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78