ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:27-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ሥጋን እንደ ዐፈር፣የሚበሩትን ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው፤

28. በሰፈራቸውም ውስጥ፣በድንኳናቸው ዙሪያ አወረደ።

29. እነርሱም እስኪጠግቡ ድረስ በሉ፤እጅግ የጐመጁትን ሰጥቶአቸዋልና።

30. ነገር ግን ገና ምኞታቸውን ሳያረኩ፣ምግቡ ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ፣

31. የእግዚአብሔር ቊጣ በላያቸው ላይ መጣ፤ከመካከላቸውም ብርቱ ነን ባዮችን ገደለ፤የእስራኤልንም አበባ ወጣቶች ቀጠፈ።

32. ይህም ሁሉ ሆኖ በበደላቸው ገፉበት፤ድንቅ ሥራዎቹንም አላመኑም።

33. ስለዚህ ዘመናቸውን በከንቱ፣ዕድሜአቸውንም በድንጋጤ ጨረሰ።

34. እርሱ በገደላቸው ጊዜ ፈለጉት፤ከልባቸው በመሻትም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።

35. እግዚአብሔር ዐለታቸው፣ልዑል አምላክ ቤዛቸው እንደሆነ አሰቡ።

36. ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት፤በአንደበታቸው ዋሹት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78