ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:24-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ይበሉም ዘንድ መና አዘነበላቸው፤የሰማይንም መብል ሰጣቸው።

25. ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፤ጠግበው እስከሚተርፍ ድረስ ምግብ ላከላቸው።

26. የምሥራቁን ነፋስ ከሰማይ አስነሣ፤የደቡብንም ነፋስ በኀይሉ አመጣ።

27. ሥጋን እንደ ዐፈር፣የሚበሩትን ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው፤

28. በሰፈራቸውም ውስጥ፣በድንኳናቸው ዙሪያ አወረደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78