ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሕዝቤ ሆይ፤ ትምህርቴን ስማ፤ጆሮህንም ወደ አንደበቴ ቃል አዘንብል።

2. አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ከጥንት በነበረ እንቈቅልሽ እናገራለሁ፤

3. ይህም የሰማነውና ያወቅነው፣አባቶቻችንም የነገሩን ነው።

4. እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።

5. ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ፤በእስራኤልም ሕግን ደነገገ፤ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፣አባቶቻችንን አዘዘ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78