ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 78:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሕዝቤ ሆይ፤ ትምህርቴን ስማ፤ጆሮህንም ወደ አንደበቴ ቃል አዘንብል።

2. አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ከጥንት በነበረ እንቈቅልሽ እናገራለሁ፤

3. ይህም የሰማነውና ያወቅነው፣አባቶቻችንም የነገሩን ነው።

4. እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።

5. ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ፤በእስራኤልም ሕግን ደነገገ፤ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፣አባቶቻችንን አዘዘ።

6. ይህም የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቅ፣እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው፣ገና ለሚወለዱት እንዲነግሩ ነው።

7. እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ አይረሱም፤ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።

8. ነገር ግን እንደ አባቶቻቸው፣እልከኞችና ዐመፀኞች፣ልቡን ያላቀና፣መንፈሱም በእግዚአብሔር የማይታመን ትውልድ አይሆኑም።

9. የኤፍሬም ልጆች የታጠቁ ቀስተኞች ቢሆኑም፣በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።

10. የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፤ በሕጉም መሠረት ለመሄድ እንቢ አሉ።

11. እርሱ የሠራውን ሥራ፣ያሳያቸውንም ድንቅ ነገር ረሱ።

12. አባቶቻቸው በዐይናቸው እያዩ፣በግብፅ አገር፣ በጣኔዎስ ምድር ታምራት አደረገ።

13. ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።

14. ቀን በደመና መራቸው፤ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 78