ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 77:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ተሰማ፤መብረቅህ ዓለምን አበራው፤ምድርም ራደች፤ ተንቀጠቀጠች።

19. መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፤መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው፤ዱካህ ግን አልታወቀም።

20. በሙሴና በአሮን እጅ፣ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 77