ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 77:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ።

2. በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ነፍሴም አልጽናና አለች።

3. አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ

4. ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።

5. የድሮውን ዘመን አሰብሁ፤የጥንቶቹን ዓመታት አውጠነጠንሁ።

6. ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ከልቤም ጋር ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦

7. “ለመሆኑ፣ ጌታ ለዘላለም ይጥላልን?ከእንግዲህስ ከቶ በጎነትን አያሳይምን?

8. ምሕረቱስ ለዘላለም ጠፋን?የገባውስ ቃል እስከ ወዲያኛው ተሻረን?

9. እግዚአብሔር ቸርነቱን ዘነጋ?ወይስ ከቍጣው የተነሣ ርኅራኄውን ነፈገ?።” ሴላ

10. እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 77