ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 76:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ

10. ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ።

11. ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተሳሉ፤ ስእለቱንም አግቡ፤በእርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ፣አስፈሪ ለሆነው ለእርሱ እጅ መንሻ ያምጡ።

12. እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል፤በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 76