ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 76:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፤ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።

2. ድንኳኑ በሳሌም፣ማደሪያውም በጽዮን ነው።

3. በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ። ሴላ

4. አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል።

5. ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ከጦረኞቹም መካከል፣እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።

6. የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ፈረስና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል።

7. መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል?

8. አንተ ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፤ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች፤

9. አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 76