ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 71:4-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።

5. ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፤ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።

6. ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።

7. ብዙዎች እንደ ጒድ አዩኝ፤አንተ ግን ጽኑ አምባዬ ነህ።

8. ቀኑን ሙሉ ክብርህን ያወራ ዘንድ፣አፌ በምስጋናህ ተሞልቶአል።

9. በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ጒልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ።

10. ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና፤ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ በአንድ ላይ አሢረዋል፤

11. እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ትቶታል፤የሚያስጥለው የለምና፣ ተከታትላችሁ ያዙት” አሉ።

12. አምላክ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤አምላኬ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

13. ባላንጣ የሆኑብኝ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ሊጐዱኝ የሚፈልጉ፣ንቀትንና ውርደትን ይከናነቡ።

14. እኔ ግን ሁል ጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፤በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።

15. አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ቀኑን ሙሉ ስለ ማዳንህ ይናገራል፤ማቆሚያ ልኩንም አላውቅም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 71