ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 71:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ከቶም አልፈር።

2. በጽድቅህ ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።

3. ምንጊዜም የምሸሽበት፣መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ።

4. አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።

5. ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፤ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።

6. ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 71