ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 71:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ከቶም አልፈር።

2. በጽድቅህ ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።

3. ምንጊዜም የምሸሽበት፣መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ።

4. አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 71