ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 7:3-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣በደልም በእጄ ከተገኘ፣

4. በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣

5. ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ፤ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል፤ክብሬንም ከዐፈር ይደባልቅ። ሴላ

6. እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!

7. የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤

8. እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፤ልዑል ሆይ፤ እንደ ቅን አካሄዴ መልስልኝ።

9. ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ጻድቅ አምላክ ሆይ፤የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ጻድቁን ግን አጽና።

10. ጋሻዬ ልዑል አምላክ ነው፤እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል።

11. እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ቍጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው።

12. ሰው በንስሓ የማይመለስ ከሆነ ግን፣ሰይፉን ይስላል፤ቀስቱን ይገትራል።

13. የሚገድሉ ጦር ዕቃዎቹን አሰናድቶአል፤የሚንበለበሉትን ፍላጻዎቹንም አዘጋጅቶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 7