ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 7:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ቍጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው።

12. ሰው በንስሓ የማይመለስ ከሆነ ግን፣ሰይፉን ይስላል፤ቀስቱን ይገትራል።

13. የሚገድሉ ጦር ዕቃዎቹን አሰናድቶአል፤የሚንበለበሉትን ፍላጻዎቹንም አዘጋጅቶአል።

14. ክፋትን እያማጠ ያለ ሰው፣ቅጥፈትን አርግዞ፣ ሐሰትን ይወልዳል።

15. ጒድጓድ ምሶ ዐፈሩን የሚያወጣ፣ባዘጋጀው ጒድጓድ ራሱ ይገባበታል።

16. ተንኰሉ ወደ ራሱ ይመለሳል፤ዐመፃውም በገዛ ዐናቱ ላይ ይወርዳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 7