ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 7:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም፤

2. አለበለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል።

3. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣በደልም በእጄ ከተገኘ፣

4. በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣

5. ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ፤ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል፤ክብሬንም ከዐፈር ይደባልቅ። ሴላ

6. እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!

7. የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤

8. እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፤ልዑል ሆይ፤ እንደ ቅን አካሄዴ መልስልኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 7