ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 69:23-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፤ጀርባቸውም ዘወትር ይጒበጥ።

24. መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤የቍጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው።

25. ሰፈራቸው ባድማ ይሁን፤በድንኳኖቻቸው የሚኖር አይገኝ፤

26. አንተ የመታኻቸውን አሳደዋልና፤ያቈሰልኻቸውንም ሥቃያቸውን አባብሰዋል።

27. በበደላቸው በደል ጨምርባቸው፤ወደ ጽድቅህም አይግቡ።

28. ከሕይወት መጽሐፍ ይደምሰሱ፤ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።

29. ነገር ግን እኔ በሥቃይና በጭንቅ ላይ እገኛለሁ፤አምላክ ሆይ፤ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ።

30. የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አወድሳለሁ፤በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

31. ከበሬ ይልቅ፣ቀንድና ጥፍር ካበቀለ እምቦሳም ይልቅ ይህ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።

32. ድኾች ይህን ያያሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤እናንተ እግዚአብሔርን የምትሹ ልባችሁ ይለምልም!

33. እግዚአብሔር ችግረኞችን ይሰማልና፤በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም።

34. ሰማይና ምድር፣ ባሕርም፣በውስጣቸውም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመስግኑት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 69