ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 68:30-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. በሸምበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኮርማ መንጋ ገሥጽ፤ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ጦርነትን የሚወዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።

31. መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፤ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

32. የምድር መንግሥታት ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ለጌታ ተቀኙ። ሴላ

33. ከጥንት ጀምሮ ከነበሩት ሰማያት በላይ ለወጣው፣በኀያል ድምፁ ለሚያስገመግመው ዘምሩ።

34. ግርማው በእስራኤል ላይ፣ኀይሉም ከደመናት በላይ ነው፣እግዚአብሔርን ብርታት የአንተ ነው በሉት።

35. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኀይልና ብርታትን ይሰጣል።እግዚአብሔር ይባረክ!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 68