ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 68:27-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. የሚመራቸው ትንሹ ብንያም ነው፤በዚያ በብዙ የሚቈጠሩ የይሁዳ መሳፍንት፣እንዲሁም የዛብሎንና የንፍታሌም መሳፍንት ይገኛሉ።

28. እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይልህን እዘዝ፤አምላክ ሆይ ቀድሞ እንዳደረግህልን አሁንም ብርታትህን አሳየን።

29. በኢየሩሳሌም ስላለው ቤተ መቅደስህ፣ነገሥታት እጅ መንሻ ያመጡልሃል።

30. በሸምበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኮርማ መንጋ ገሥጽ፤ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ጦርነትን የሚወዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።

31. መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፤ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

32. የምድር መንግሥታት ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ለጌታ ተቀኙ። ሴላ

33. ከጥንት ጀምሮ ከነበሩት ሰማያት በላይ ለወጣው፣በኀያል ድምፁ ለሚያስገመግመው ዘምሩ።

34. ግርማው በእስራኤል ላይ፣ኀይሉም ከደመናት በላይ ነው፣እግዚአብሔርን ብርታት የአንተ ነው በሉት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 68