ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 68:21-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. በእርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፣በኀጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጒራም አናት ይፈነካክታል።

22. ጌታ እንዲህ ይላል፤ “ከባሳን መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ከባሕርም ጥልቀት አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤

23. እግርህ በጠላትህ ደም ውስጥ እንዲጠልቅ፣የውሻህም ምላስ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው።”

24. አምላክ ሆይ፤ የክብር አካሄድህ ታየ፤ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገው የክብር አካሄድ ነው።

25. መዘምራን ከፊት፣ መሣሪያ የሚጫወቱ ከኋላ ሆነው ሲሄዱ፣ከበሮ የሚመቱ ቈነጃጅትም በመካከላቸው ነበሩ።

26. እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት፤ ከእስራኤል ምንጭ የተገኛችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ።

27. የሚመራቸው ትንሹ ብንያም ነው፤በዚያ በብዙ የሚቈጠሩ የይሁዳ መሳፍንት፣እንዲሁም የዛብሎንና የንፍታሌም መሳፍንት ይገኛሉ።

28. እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይልህን እዘዝ፤አምላክ ሆይ ቀድሞ እንዳደረግህልን አሁንም ብርታትህን አሳየን።

29. በኢየሩሳሌም ስላለው ቤተ መቅደስህ፣ነገሥታት እጅ መንሻ ያመጡልሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 68