ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 68:14-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ሁሉን ቻዩ በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣በሰልሞን እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው።

15. አንተ ብርቱ ተራራ፣ የባሳን ተራራ ሆይ፤አንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራራ፣ የባሳን ተራራ፤

16. እናንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፤እግዚአብሔር ሊኖርበት የመረጠውን ተራራ፣በእርግጥ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚኖርበትን ተራራ ለምን በምቀኝነት ዐይን ታያላችሁ?

17. የእግዚአብሔር ሠረገላዎች እልፍ አእላፍ ናቸው፤ሺህ ጊዜም ሺህ ናቸው፤ጌታ ከሲና ወደ መቅደሱ ገባ።

18. ወደ ላይ ዐረግህ፤ምርኮ አጋበስህ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ አንተ በዚያ ትኖር ዘንድ፣ከዐመፀኞችም ሳይቀር፣ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ።

19. ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ። ሴላ

20. አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ከሞት ማምለጥ የሚቻለውም በጌታ በእግዚአብሔር ነው።

21. በእርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፣በኀጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጒራም አናት ይፈነካክታል።

22. ጌታ እንዲህ ይላል፤ “ከባሳን መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ከባሕርም ጥልቀት አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤

23. እግርህ በጠላትህ ደም ውስጥ እንዲጠልቅ፣የውሻህም ምላስ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 68