ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 68:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ጌታ እንዲህ ሲል ቃሉን አስተላለፈ፤ትእዛዙን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፤

12. “የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ።

13. በበጎች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ፣ከብር እንደ ተሠሩ የርግብ ክንፎች፣በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ።”

14. ሁሉን ቻዩ በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣በሰልሞን እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው።

15. አንተ ብርቱ ተራራ፣ የባሳን ተራራ ሆይ፤አንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራራ፣ የባሳን ተራራ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 68