ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 68:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ይነሣ፤ ጠላቶቹ ይበተኑ፤የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።

2. ጢስ እንደሚበንን፣እንዲሁ አብንናቸው።ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።

3. ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤በእግዚአብሔር ፊት ሐሤት ያድርጉ፤ደስታንና ፍስሓን የተሞሉ ይሁኑ።

4. ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም ተቀኙ፤በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፤ስሙ እግዚአብሔር በተባለው ፊት፣እጅግ ደስ ይበላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 68