ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 66:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ፍሪዳዎችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣አውራ በጎችንም የሚጤስ ቍርባን አድርጌ አቀርብልሃለሁ፤ኰርማዎችንና ፍየሎችንም እሠዋልሃለሁ። ሴላ

16. እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ ኑና ስሙ፤ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።

17. በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤በአንደበቴም አመሰገንሁት።

18. ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ጌታ ባልሰማኝ ነበር።

19. አሁን ግን እግዚአብሔር በእርግጥ ሰምቶኛል፤ጸሎቴንም አድምጦአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 66