ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 65:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤ቦይዋን ታስተካክላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ቡቃያዋንም ትባርካለህ።

11. ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል።

12. የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።

13. ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 65