ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 65:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ለአንተ የተሳልነውን እንፈጽማለን።

2. ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፤የሰው ልጆች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ።

3. ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።

4. አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣በአደባባይህም ያኖርኸው ምስጉን ነው!ከተቀደሰው መቅደስህ፣ከቤትህም በረከት እንረካለን።

5. እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ።

6. ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ኀይልንም ታጥቀሃል።

7. አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣የማዕበላቸውን ፉጨት፣የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።

8. ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 65