ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 62:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።

7. መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው።

8. ሰዎች ሆይ፤ ሁል ጊዜ በእርሱ ታመኑ፤ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ

9. ከተናቀ ወገን መወለድ ከንቱ፣ከከበረውም መወለዱ ሐሰት ነው።በሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም፣ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው።

10. በዝርፊያ አትታመኑ፤በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤በዚህ ብትበለጽጉም፣ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 62