ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 62:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?

4. ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤በአፋቸው ይመርቃሉ፤በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ

5. ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና።

6. ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።

7. መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው።

8. ሰዎች ሆይ፤ ሁል ጊዜ በእርሱ ታመኑ፤ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ

9. ከተናቀ ወገን መወለድ ከንቱ፣ከከበረውም መወለዱ ሐሰት ነው።በሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም፣ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 62