ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 62:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው።

2. ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።

3. ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?

4. ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤በአፋቸው ይመርቃሉ፤በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ

5. ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 62